የኦሮሚያ የቱሪዝም ሳምንት ከመስከረም 20 - 22 ቀን 2018 ዓ.ም እንደሚካሄድ የኦሮሚያ ክልል ቱሪዝም ኮሚሽን አስታወቀ።
የኦሮሚያ ክልል ቱሪዝም ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ነጋ ወዳጆ በሰጡት መግለጫ፤ የቱሪዝም ሳምንቱ በክልሉ የሚገኙ የቱሪዝም ፀጋዎችን ለማስተዋወቅ ብሎም የቱሪስት ፍሰትን በመሳብ ረገድ ጉልህ ሚና ይኖረዋል ብለዋል።
ለ5ኛ ጊዜ በሚካሄደው የቱሪዝም ሳምንት በኢትዮጵያ የሚገኙ የቱሪዝም መዳረሻዎች እና ባህላዊ ትውፊቶች እንደሚተዋወቁ ገልጸዋል።
በአዲስ አበባ በሚዘጋጀው የቱሪዝም ሳምንት ላይ ከአፍሪካ ሀገራት የሚመጡ እንግዶች እንዲታደሙ ጥሪ መደረጉን ተመላክቷል።
በቱሪዝም ሳምንቱ የተለያዩ የውይይቶች መድረኮች፣ የኦሮሚያ ቱሪዝም ሽልማት፣ የቁንጅና ውድድር እና ሌሎች መሰናዶዎች ይካሄዳሉ ተብሏል።