Search

የሕዳሴ ግድብን መጎብኘት ይፈልጋሉ?

ቅዳሜ መስከረም 10, 2018 89

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ምረቃ ሥነ-ሥርዓት ላይ ባደረጉት ንግግር ሕዳሴ ግድብ የሁሉም ኢትዮጵያውያን አሻራ ያረፈበት እንደመሆኑ ሁሉም ሊጎበኘው ይገባል ብለው እንደነበር ይታወሳል።
በዚሁ መሠረት ግድቡን መጎብኘት የሚፈልጉ ቡድኖች እና ተቋማት ከሰኞ መስከረም 12 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ መመዝገብ እንደሚችሉ የቱሪዝም ሚኒስትር ሰላማዊት ካሳ አስታውቀዋል።
ይህም የአንድ ቀን የደርሶ መልስ ጉብኝት እንደሚሆን ጠቁመው፤ ፍላጎቱ ያላቸው ዜጎች በባለ 50 ሰው ቡድን በመደራጀት በኢትዮጵያ አየር መንገድ በኩል መስተናገድ እንደሚችሉ ገልጸዋል።
ለወደፊቱ በሕዳሴ ግድብ ዙሪያ ለቱሪስቶች አስፈላጊ የሆኑ መሠረተ ልማቶችን ለማሟላት እንደሚሠራም አመላክተዋል።
ለጊዜው ግን ፍላጎቱ ያላቸው ድርጅቶች በጉብኝቱ በመሳተፍ ምርት እና አገልግሎታቸውን ማቅረብ እንደሚችሉ ተናግረዋል።
ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብን የማየት አጋጣሚ ያገኙ በርካታ የሀገር ውስጥ እና የውጭ ዜጎች ግድቡ ሊጎበኝ የሚገባው ግዙፍ ፕሮጀክት ስለመሆኑም በተለያዩ ጊዜያት ገልጸዋል።
 
በሰናይት ብርሀኔ