Search

ለ15 ዓመታት ከኖሩበት ፓሪስ ወደ ሀገራቸው ተመልሰው በቴምር ልማት ውጤታማ የሆኑት ሰኢድ ሐጂ የሱፍ

እሑድ መስከረም 11, 2018 46

አቶ ሰኢድ ሐጂ የሱፍ ፈረንሳይ፣ ፓሪስ ትዳር መስርተው ለ15 ዓመታት ኖረዋል።

በፓሪስ የተዋወቋቸው እና ከእርሳቸው የተሻለ ኑሮ የሚኖሩ ጓደኞቻቸው በሀገራቸው የቴምር ልማት እያሠሩ ተጨማሪ ገቢ እንደሚያገኙ ሲያጫውቷቸው፤ እኔስ በሀገሬ ያለኝን መሬት ለምን አልሰራበትም በማለት ወደ ኢትዮጵያ ይመጣሉ።

ከዚያም በአፋር በውርስ ከአባታቸው ባገኙት 130 ሄክታር መሬት ላይ ቴምር እና የተለያዩ ተክሎችን በማልማት ቤተሰባቸውን ማስተዳደር ይጀምራሉ።

አቶ ሰኢድ በአሁኑ ወቅት በማሳቸው ላይ ቴምር፣ ስንዴ፣ ሽንኩርት እና በርበሬ ከማልማት በተጨማሪ የእንስሳት እርባታ ሥራም ያከናውናሉ።

በዚህም ከ100 በላይ ለሚሆኑ የአካባቢው ወጣቶች የሥራ ዕድል መፍጠር ችለዋል።

የሰው ልጅ ጠንክሮ ከሠራ መሰደድ ሳያስፈልገው ባለበት ሆኖ ኑሮውን ማሻሻል ይችላል የሚሉት አቶ ሰኢድ፤ ሕይወታችንን ለመቀየር የሚያስፈልገን ያለንን ሀብት ለይተን በማወቅ  በአግባቡ መጠቀም ብቻ ነው ሲሉ ይገልፃሉ።

አቶ ሰኢድ ሐጂ የሱፍ በቅርቡ በአፋር፣ ሰመራ በተዘጋጀው ዓለም አቀፍ የቴምር ፌስቲቫል በምርጥ ቴምር ዘርፍ አሸናፊ ነበሩ።

በቢታንያ ሲሳይ

#EBCdotstream #entrepreneurship #agriculture #datepalm