Search

በሕዳሴ ግድብ የታየውን አንድነት በመጠቀም የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅሞች ማስጠበቅ ይገባል - ከንቲባ ከድር ጁሀር

ሰኞ መስከረም 12, 2018 170

በታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የታየውን አንድነት ይበልጥ በመጠቀም የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅሞች ማስጠበቅ እና የኢትዮጵያን ዕድገት ማስቀጠል ይገባል ሲሉ የድሬዳዋ ከተማ ከንቲባ ከድር ጁሀር ተናገሩ።
የሕዳሴ ግድብ መጠናቀቁን አስመልክቶ በድሬዳዋ ከተማ ስቴዲየም ሕዝባዊ የድጋፍ እና የደስታ መግለጫ ሰልፍ እየተካሄደ ነው።
 
በወቅቱ ከንቲባ ከድር ጁሀር በግድቡ የታየውን አንድነት በሌሎች ሀገራዊ ፕሮጀክቶች መድገም ይገባል ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል።
የድሬዳዋ ሕዝብ ለታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ መጠናቀቅ ድጋፍ ሲያደርግ መቆየቱን አስታውሰው፤ የግድቡ ግንባታ የሕብረ ብሔራዊ አንድነታችን ማሳያ ነው ሲሉ ተናግረዋል።
በተያያዘም በድሬዳዋ በቀጣይ 8 ቢሊየን ብር በጀት የተያዘላቸው ግዙፍ ፕሮጀክቶችን ለማስጀመር እና ለማጠናቀቅ እቅድ መያዙን ተናግረዋል።
በቀጣይም በሕዳሴ ግድቡ መጠናቀቅ የታየውን መነሳሳት በሌሎች ዘርፎችም መድገም ይገባል ብለዋል።
የድጋፍ ሰልፈኞቹ በግድቡ መጠናቀቅ የተሰማቸውን ደስታ ገልፀዋል።
 
በቶማስ ሀይሉ