በኢፌዲሪ ፕሬዚዳንት ታየ አፅቀ ሥላሴ የተመራ የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን በ80ኛው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (የ.ተ.መ.ድ.) ጠቅላላ ጉባዔ ይፋዊ መክፈቻ ሥነ-ሥርዓት ላይ እየተሳተፈ ይገኛል።
በመክፈቻ ሥነ ሥርዓቱ ላይ ንግግር ያሰሙት የተመድ ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ፤ ዓለማችን በተለያዩ የሠላም እና ፀጥታ ጉዳዮች፣ ድህነት፣ ረሀብ፣ ጦርነት፣ የአየር ንብረት ለውጥ፣የኢኮኖሚ ቀውስ እየተፈተነች ባለበት ወቅት የሚከበረው የተመድ 80ኛ ዓመት ፤ አባል ሀገራት ከመቼውም ጊዜ በላይ አብሮነታቸውን በማጠናከር የተሻለች ዓለም ለመፍጠር በጋራ መሥራት እንደሚገባቸው አሳስበዋል።

የተመድ ሥርዓት እና መዋቅር 21ኛውን ክፍለ ዘመን በሚመጥን ልክ መለወጥ እንደሚገባ ገልፀዋል።
ዋና ፀሐፊው የዓለም ኀብረተሰብ ምርጫውን ሠላም፣ ፍትህ ዘላቂ ልማት እና ሰብዓዊ ክብር ሊያደርግ እንደሚገባና ለተግባራዊነቱም ቁርጠኝነት እንዲያሳይ ጥሪ አቅርበዋል።