በአሜሪካ ኒውዮርክ እየተካሄደ ካለው 80ኛው የተመድ ጠቅላላ ጉባዔ ጎን ለጎን አራተኛው የብሪክስ አባል ሀገራት ዋና አስተባባሪዎች እና ምክትል አስተባባሪዎች ስብሰባ ተካሂዷል።
የስብሰባው ዓላማ በቀጣይ በሚደረገው ጉባዔ ላይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በሚሰጡት የጋራ የመገናኛ ብዙኃን መግለጫ ላይ ያተኮረ ነው።
በስብሰባው ላይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ልዩ የፖሊሲ አማካሪ አምባሳደር ምኒልክ ዓለሙ ብራዚል በብሪክስ ፕሬዚዳንትነቷ ያከናወነቻቸውን ተግባራት በማድነቅ፤ ኢትዮጵያ እ.አ.አ. በ2026 የሕንድን የብሪክስ ሊቀመንበርነት እንደምትደግፍ አሳውቀዋል።