Search

በደመራ ማብራት ሥነ-ሥርዓት ወቅት የኤሌክትሪክ አደጋ እንዳይከሰት መደረግ የሚገባው ጥንቃቄ

ረቡዕ መስከረም 14, 2018 34

የደመራ ማብራት ሥነ-ሥርዓትን ከኤሌክትሪክ ምሰሶዎች፣ ትራንስፎርመሮች እና ማስተላለፊያ መስመሮች በበቂ ርቀት በማከናወን አደጋን መከላከል እንደሚገባ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ጠቁሟል።

በተለይ በበዓላት ወቅት የሚከናወኑ ተግባራትን ከኤሌክትሪክ መሠረተ ልማቶች ጋር ንክኪ በሚፈጥር መልኩ ማከናወን በሰውና በንብረት ላይ ከፍተኛ አደጋ ሊያስከትል እንደሚችል ነው ተቋሙ ያስጠነቀቀው። 

ለአደጋ መንስዔ የሚሆኑ መሠረተ ልማቶችን አስቀድሞ በመለየት የእንጨት ምሰሶዎችን በኮንክሪት መቀየር እና ያልተሸፈኑ መስመሮችን በሽፍን ገመድ መተካትን ጨምሮ የቅድመ ጥንቃቄ ሥራዎች እየተከናወኑ ነው ተብሏል።

በመስቀል በዓል የኃይል መቆራረጥ እንዳይኖር ለማድረግ፤ የኃይል መቆራረጥ ካጋጠመም አፋጣኝ ምላሽ ለመስጠት አስፈላጊው ቅድመ ዝግጅት ስለመደረጉም ተገልጿል።

ድንገት የኤሌክትሪክ አደጋ ካጋጠመ በነፃ የስልክ መስመር 905 ወይም 904 በፍጥነት በመደወል ጥቆማ መስጠት እንደሚገባም አገልግሎቱ አሳስቧል።

በላሉ ኢታላ

#EBCdotstream #EEU #Meskel