Search

“ድሬ - መሶብ” የአንድ ማዕከል አገልግሎት ተጀመረ

ሓሙስ መስከረም 15, 2018 204

በቴክኖሎጂ የታገዘ ቀልጣፋ አገልግሎትን ለመስጠት የሚያስችለው “ድሬ - መሶብ” የአንድ ማዕከል አገልግሎት በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት ሆኗል።
በመጀመሪያው ምዕራፍ በአንድ ማዕከል አገልግሎቱ ውስጥ 6 የከተማ አስተዳደሩ እና 4 የፌዴራል የመንግሥት የልማት ድርጅቶች የገቡ ሲሆን፤ የተለዩ 28 አገልግሎቶች በማዕከሉ የሚሰጡ ይሆናል ተብሏል።
በማዕከሉ ሥራ ማስጀመሪያ መርሀ-ግብር ላይ የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ከድር ጁሀር፣ በሚኒስትር ማዕረግ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ኃላፊ እናትዓለም መለሰ፣ የሐይማኖት አባቶች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
 
በቶማስ ሀይሉ