Search

የርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት

ዓርብ መስከረም 16, 2018 38

እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ አደረሳችሁ፤ አደረሰን።
ተፈጥሮ ምድርን ደማቅና ውብ አድርጎ በሚያሸበርቅበት የአዲስ ዓመት ማግስት የሚከበረው የመስቀል በዓል ሃይማኖታዊ አስተምህሮው እና ማህበራዊ ትውፊቶቹ ለአዳዲስ ስኬቶች የሚያነሳሱ ናቸው።
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልልም መስቀል ከሃይማኖታዊ እሴቶቹ ባሻገር ማህበራዊ ትሩፋቶቹ በርካታ ናቸው። ተራርቀው የሰነበቱ ቤተሰቦች ተገናኝተው ቤተሰባዊ ፍቅራቸውን የሚወጡበት፣ ሐሴታቸውን የሚገልጹበት ነው።
የተስፋ ብርሃን፣ የፅናት፣ የአሸናፊነት እና የመስዋዕትነት ምልክት የሆነው የመስቀል በዓል፤ የአብሮነት፣ የተስፋ እና የትጋት እሴቶችን እንድናጠናክር የሚያግዝ ነው።
በዓሉ የአብሮነት እሴቶችን ለማጎልበት፣ ለሰላም ግንባታና ለልማት በአጠቃላይ ለሁለንተናዊ ብልፅግና በጋራ ለመትጋት የምንነሳሳበት እንዲሆን እመኛለሁ። መልካም የመስቀል በዓል!
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)