መተሳሰብን፣ ኅብረትን፣ አንድነትን እና መሰብሰብን የሚያጎላው የመስቀል ደመራ በመላው ኢትዮጵያ እየተከበረ ይገኛል።

ደመራ ማለት መጨመር፣ መደመር፣ መሰብሰብ፣ መከመር ነው። አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ "ደመራ" የሚለውን ቃል "ደመረ" ከሚለው የግዕዝ ግስ የተገኘ ቃል መሆኑን ያብራራሉ።

አለቃ ኪዳነ ወልድ "ደመራ" ግእዝ እና አማርኛን ያስተባበረ ቃል መሆኑን ጠቅሰው፣ በመስቀል በዓል ዋዜማ እንጨቶች የሚደመሩበት መሆኑን አስረድተዋል።

መስቀል ከሃይማኖታዊ በዓልነቱም ባሻገር በባህላዊ ትውፊቱ በመላው ኢትዮጵያ የሚናፈቅ በዓል ስለሆነ ከሰሜን እስከ ደቡብ፣ ከምሥራቅ አስከ ምዕራብ ያለው የኢትዮጵያ ሕዝብ የሚያከብረው ነው።
ለዚህም ነው በማይዳሰስ ቅርስ ዘርፍ በዩኔስኮ የዓለም ቅርስነት ተመዝግቦ ኢትዮጵያ ለመላው ዓለም ያበረከተችው ስጦታ የሆነው።
በለሚ ታደሰ