እንኳን ለደመራ እና መስቀል በዓል በሰላም አደረሰን፤ አደረሳችሁ።
የከተማችን ልዩ ድምቀት ለሆነው እና በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የትምህርት፣ ሳይንስ እና ባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) በማይዳሰስ ቅርስነት የተመዘገበው የመስቀል ደመራ በዓል በመስቀል አደባባይ በታላቅ ድምቀት እየተከበረ ነው።
ለመላው የኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች እንኳን በሰላም አደረሳችሁ እያልኩ፤ በዓሉ የአብሮነት፣ የፍቅር እና የሰላም እንዲሆንላችሁ እመኛለሁ። መልካም በዓል!
የአዲስ አበባ ከንቲባ አዳነች አቤቤ