Search

የከንቲባ ከድር ጁሀር የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት

ዓርብ መስከረም 16, 2018 51

እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ አደረሳችሁ።
የዘንድሮውን የመስቀል በዓል የምናከብረው ታላቁ የሕዳሴ ግድባችንን በህዝባችን የተደመረ አቅም በድል አጠናቅቀን፤ በስኬት ከተስፋ ወደ ሚጨበጥ ብርሃን በተሸጋገርንበት የማንሰራራት ዘመን መሆኑ በዓሉን ለየት ያደርገዋል።
መስቀል የፍቅር፣ የሰላም እና የአብሮነት በዓል እንደመሆኑ እርስ በርስ በመተሳሰብ፣ ለዘላቂ ሰላም መረጋገጥ በመሥራት፣ አንድነትን በማፅናት የድሬዳዋ እሴቶቻችን ደምቀው የሚታዩበት ይሆናል።
ህብረተሰቡ የተለመደ የመተጋገዝ ባህሉን በመተግበር በዓሉን ከሌሎች ወንድም እህቶቹ ጋር በጋራ ሊያከብረው ይገባል።
በዓሉ የሰላም፣ የፍቅር እና የአብሮነት እንዲሆን እመኛለሁ፤ መልካም የደመራና መስቀል በዓል ይሁንልን።
የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ከድር ጁሀር