የባህል እና ስፖርት ሚኒስትር ወ/ሮ ሸዊት ሻንካ በመስቀል አደባባይ በተካሄደው የደመራ ሥነ-ሥርዓት ላይ ንግግር አድርገዋል፡፡
የመስቀል ደመራ ሥነ-ሥርዓት የኢትዮጵያን ብዝኃ ባህል፣ ቋንቋ፣ እሴት እና ሐይማኖትን የሚያንጸባርቅ ድንቅ ሥርዓት ነው ብለዋል ሚኒስትሯ፡፡
ኢትዮጵያ ችቦ ለመስራት በአንድነት እንደተገመዱት እንጨቶች ሁሉ በርካታ ባህሎች፣ እምነቶች እና ውብ እሴቶችን የያዘች ሀገር መሆኗንም ሚኒስትሯ አንስተዋል።

ኢትዮጵያ ካሏት ፀጋዎች መካከል አንዱ የመስቀል በዓል አከባበር መሆኑን ያወሱት ወ/ሮ ሸዊት፣ ኢትዮጵያ በትውልድ ቅብብሎሽ ለዘመናት የዳበረ እምቅ ሀብት ያላት ታሪካዊ ምድር እንደሆነችም ነው የተናገሩት፡፡
የዘንድሮ የመስቀል በዓል ኢትዮጵያ በርካታ ችግሮችን አልፋ ማንሰራራት የጀመረችበት ወቅት ላይ መከበሩ ልዩ ያደርገዋልም ብለዋል ሚኒስትሯ፡፡
የተጀመረውን ጉዞ ከዳር ለማድረስ በአንድነት መነሳት ይገባናል ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
በሜሮን ንብረት