ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ትውልድን ከትውልድ የሚያገናኝ ድልድይ ነው ሲሉ የምጣኔ ሀብት ባለሙያው ፀጋዬ ደግነህ (ዶ/ር) ይገልጻሉ።
የግድቡ መጠናቀቅ በተለያየ ዘመን የነበሩ ትውልዶችን ህልም እውን ማድረግ ያስቻለ ነው ይላሉ።
ሕዳሴ ቀጣዩን ትውልድ ለተሻለ ሥራ የሚያነሳሳ ታላቅ ፕሮጀክት መሆኑንም ነው የተናገሩት።
ግድቡን በተመለከተ በጀርመን የሚገኙ አንዳንድ ሚዲያዎች የተዛባ መረጃዎችን ሲያስተላልፉ እንደነበር አስታውሰው፤ በዚያ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ዘገባዎቹ ሚዛናዊነት እንዲኖራቸው በኅብረት በመስራት የተሳሳቱ መረጃዎችን ማስቀየራቸውን አይዘነጉትም።
ይህ ኅብረት በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ምን ጊዜም በሀገራዊ ጉዳይ ላይ ቀናዒ ምኞት እንዳላቸው ማሳያ ነው ይላሉ።
ግድብ ሲመረቅም ዓለም አቀፍ ሚዲያዎች ኢትዮጵያ የገነባችው የአፍሪካ ትልቁ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ግድብ እያሉ ሰፊ ሽፋን ሰጥተውታል፤ ይህ ደግሞ ለተጨማሪ ሥራ የሚያነሳሳን ነው ይላሉ።
ከዚህ በፊት ስለኢትዮጵያ ጥሩ የማይዘግቡ የውጭ ሚዲያዎች ጭምር የሕዳሴ ግድብ መጠናቀቁን ተከትሎ በጎ ዘገባ መስራታቸው፣ በኅብረት ከሰራን ዓለም የኢትዮጵያ በጎ ጎን በአግባቡ እንደሚገነዘብ ማሳያ ነው ብለዋል።
በቢታኒያ ሲሳይ
#EBC #ebcdotstream #GERD