Search

ኢቢሲ ለአንጋፋዋ ጋዜጠኛ አስካለ ተስፋዬ ልዩ እውቅና ሰጠ

ቅዳሜ መስከረም 17, 2018 28

የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (ኢቢሲ) ለአንጋፋዋ ጋዜጠኛ አስካለ ተስፋዬ ልዩ እውቅ ሰጥቷል

‹‹ውሎ አዳር›› በተሰኘው ሪያሊቲ ሾው ኢትዮጵያን፣ ህዝቦቿን እና ባህሎቿን በሚገባ በማስተዋወቋ፣ ለህዝቦች አብሮነት መጠናከር እና ለቱሪዝም ዕድገት በአርአያነት የሚወሰድ ፋይዳ ያላቸው ፕሮግራሞችን ለህዝብ በማቅረቧ እውቅና ሰጥተናታል ብሏል ተቋሙ

የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽንን በመወከል ሽልማቱን ያበረከቱት የኢቢሲ  ዋና አስፈፃሚ /ቤት ሃላፊ አቶ ሞላልኝ መለሰ ናቸው።

አቶ ሞላልኝ፥ ‹‹ውሎ አዳር›› ዝግጅት በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ብሔር ብሔረሰቦች ያላቸውን ቱባ ባሕል ሁሉም እንዲያውቅ በማድረግ ረገድ ትልቅ ሚና እንደነበረው ገልጸው፤ ለስኬታማነቱ የጋዜጠኛዋ አስካለ ተስፋዬ ሚና የላቀ እንደነበር ተናግረዋል።

አንጋፋዋ ጋዜጠኛ በምትሠራበት ተቋም እውቅናና ሽልማት ማግኘቷ ከሌሎቹ ሽልማቶች የተለየ ስሜት እንደፈጠረባት ገልፃለች።

ኢቢሲ በፈጠረልኝ ፕሮግራም ከኢትዮጵያ ህዝብ በርካታ ሽልማትና ፍቅር አግኝቼበታለሁ፤ ተቋሜ የሰጠኝ ይህብር እኔን የበለጠ እንድሰራ የሚያበረታታኝ፣ ሥራቸውን አክብረው የሚተጉ ጋዜጠኞች ሁሉ ነገ ይህ እውቀና እንደሚጠብቃቸውም መልዕክት የሚያስተላልፍ ነው ብላላች።

አክላም፥ በሥራዋ ሁሉ አብረዋት የደከሙ የካሜራ እና ሌሎቹ ባለሙያዎችን እንዲሁም የተቋሙን ሃላፊዎች እመስግናለች።

አንጋፋው ጋዜጠኛ ዓለምነህ ዋሴን ጨምሮ በተለያየ የሥራ አጋጣሚ ከእርሷ ጋር ያሳለፉ ባለሙያዎች ስለ ጋዜጠኛዋ እማኝነታቸውን የሰጡ ሲሆን፤ የሥራ ትጋቷ፣ መስላ ሳይሆን ሆና መሥራቷ እና በከፍተኛመም ውስጥ እያለች ጭምር ለሙያዋ እና ለተቋሟ የከፈለችው መስዋዕትነት መገለጫዎቿ እንደሆኑ ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (ኢቢሲ) በኤፍ ኤም አዲስ 97.1 እና በኢቲቪ መዝናኛ በተላለፈው 2018 የመስቀል በዓል ዝግጅት ለአንጋፋዋ ጋዜጠኛ አስካለ ተስፋዬ ልዩ እውቅና ሲሰጥ ካባ ማልበስን ጨምሮ ዋንጫና የምስክር ወረቀት አበርክቶላታል።

በናትናኤል ሀብታሙ

#EBC #EBCdotstream #ETV #Recognition #AskaleTesfaye