Search

በ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ከፍተኛ ውጤት ላመጡ ተማሪዎች የማበረታቻ ሽልማት ተሰጠ

ሰኞ መስከረም 19, 2018 76

በአማራ ክልል በ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ከፍተኛ ውጤት ያመጡ ተማሪዎች የሽልማት ሥነ-ሥርዓት በባህርዳር ከተማ ተካሂዷል።

በክልሉ በ2017 የትምህርት ዘመን በተሰጠው የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና 452 ተማሪዎች ከ500 በላይ ውጤት አስመዝግበዋል።

በመርሐ-ግብሩ ለተማሪዎች በውጤት ደረጃ ከ30 ሺህ ብር ጀምሮ የማበረታቻ የገንዘብ ሽልማት እና የምስክር ወረቀት ተሰጥቷል።

በሽልማቱ ሴቶች ልዩ ሽልማት ጭምር የተበረከተላቸው ሲሆን፤ ከ400 በላይ ውጤት ያገኙ ሁለት ዓይነ ስውራንም እውቅና እና ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።

በእውቅና መርሐ-ግብሩ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳደር አብዱ ሁሴንን (ዶ/ር) ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ሀላፊዎች፣ የትምህርት ዘርፍ ተዋናዮች፣ መምህራን፣ ተማሪዎች እና ወላጆች ተገኝተዋል።

በራሔል ፍሬው

#EBCdotstream #Education #Bahirdar #12thgrade

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ:

ተያያዥ ዜናዎች: