Search

የክብር ዶክትሬትን በመጠሪያነት መጠቀም አይቻልም - የትምህርት ሚኒስቴር

ዓርብ ኅዳር 05, 2018 125

የህዝብ ተወካዮች የሰው ሃብት ልማት ሥራ ስምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በዛሬው ዕለት የትምህርት ዘርፉን 1 ሩብ ዓመት ሥራ አፈፃፀም ተመልክቷል።

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በዚሁ ወቅት፥ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የክብር ዶክትሬት አሰጣጥን የወጥነት ችግር እንደነበረበት አንስተዋል።

በክብር ዶክትሬት አሰጣጡ ወጥ አሠራር መከተል በማስፈለጉ ሀገራዊ መመሪያ ተዘጋጅቶ ለትግበራ ዝግጁ መሆኑን ገልጸዋል።

በመሆኑም ከዚህ በኋላ ሁሉም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የክብር ዶክትሬት አሰጣጥን በመመሪያው መሠረት መፈጸም እንደሚኖርባቸው ጠቁመዋል።

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የክብር ዶክትሬት ማዕረግ ለመስጠትመመሪያው የተቀመጡ ሀገራዊ እና ዓለም አቀፍ መስፈርቶችን ማሟላት አለባቸው ብለዋል።

በሙያው የተለየ ሥራ ያበረከተ ኢትዮጵያዊም ሆነ ሌላ ዜጋ በመመሪያው የተዘረዘረውን መስፈርት የሚያሟላ ከሆነ የክብር ዶክትሬት ማዕረግ ማግኘት እንደሚችል ገልጸዋል።

ይሁን እንጂ የተሰጠውን የክብር ዶክትሬት ለመጠሪያነት መጠቀም እንደማይቻል ተናግረዋል።

#ebcdotstream #moe #hpr #universities #honorarydoctorate