Search

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግቢያ ውጤት ከ300 ነጥብ ወደ 297 ዝቅ ተደርጓል - ትምህርት ሚኒስቴር

ረቡዕ መስከረም 21, 2018 58

ትምህርት ሚኒስቴር የ2017 ዓ.ም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግቢያ ውጤትን ከ300 ወደ 297 ዝቅ አድርጓል፡፡
ሚኒስቴሩ ከዚህ ቀደም ነጥባቸው ከ 300 በላይ ወይም በመቶኛ ከ 50 በመቶ በላይ ያስመዘገቡ ተማሪዎች ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እንዲቀላቀሉ ተደርጎ እንደቆየ ይታወሳል።
ሚኒስቴሩ ለኢቢሲ ዶትስትሪም በሰጠው መረጃ፤ በ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና አማካይ ውጤታቸው 49.5 እስከ 49.99 በመቶ ያመጡ ተማሪዎች ውጤታቸው ወደ 50 በመቶ እንዲጠጋጋ መወሰኑን አመልክቷል፡፡
ይህን ተከትሎም ውጤታቸው ከ297 በላይ ወይም በመቶኛ 49.5 በመቶ በላይ ያስመዘገቡ ተማሪዎች፤ ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተቀላቅለው መማር እንደሚችሉ የትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል።
በሰለሞን ከበደ