የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) ከኖርዌይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኢስፔን ባርዝ ኢየድ እና ከዴንማርክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ሎት መሻን ጋር ውይይት አድርገዋል።
ውይይቱ በኢትዮጵያ ንጹህ የኃይል ፕሮጀክቶች፣ የደን ልማት እና ቀጣናዊ የደኅንነት ሁኔታ ዙሪያ እንዲሁም የኖርዲክ አካባቢ አገራት በኢትዮጵያ ያላቸው የኢንቨስትመንት ተሳትፎ ላይ ያተኮረ ነው።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) ኢትዮጵያ ከኖርዌይ እና ከዴንማርክ ጋር የቆየ አጋርነት እንዳላት ገልጸው፤ የዛሬው ውይይትም ግንኙነቱን የበለጠ ለማጠናከር ዕድል የፈጠረ መሆኑን አንስተዋል።
#EBCdotstream #Ethiopia #MFA #Norway #Denmark