Search

ወደ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የተቀላቀሉ ተማሪዎች ቁጥር 52 ሺህ 279 ሆነ

ሓሙስ መስከረም 22, 2018 42

የፈተና ውጤታቸው በመቶኛ 49.5 በመቶ እና ከዚያ በላይ የሆነ እንዲሁም፤ የፊዝክስ ውጤት ወደ መቶኛ ያልተቀየረላቸው እና ወደ መቶኛ ሲቀየር በነጥብ ቤት የነበሩ ቁጥሮች ያልተደመረላቸው ተማሪዎች ተስተካክሎላቸዋል ብሏል የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት።
በመሆኑም በአጠቃላይ 3ሺህ 350 ተጨማሪ ተማሪዎች ዝቅተኛውን የማለፊያ ውጤት ማስመዝገብ ችለዋል፡፡
በዚሁ መሠረት የ2017 ትምህርት ዘመን ላይ 50 ከመቶና በላይ ያመጡ አጠቃላይ ተፈታኞች 52 ሺህ 279 ሆነው የተመዘገቡ ሲሆን፤ በአጠቃላይ በመቶኛ ሲገለጽ ወደ 8.9 በመቶ ሆኖ ተመዝግቧል።
የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት የተፈታኞችን ውጤት የገለጸ ሲሆን፤ ተፈታኞች በተገለጸው ውጤታቸው እና ተያያዥ መረጃዎች ላይ ቅሬታቸውን በተሰጣቸው የጊዜ ገደብ ውስጥ አቅርበዋል።
የቅሬታ አቅራቢዎች ብዛት በከፍተኛ ደረጃ ከዓመት ዓመት እየቀነሰ መጥቷል ያለው ተቋሙ፤ በ2017 ላይ በበይነ መረብ በተፈተኑ በተወሰኑ ተማሪዎች ላይ የፊዝክስ ውጤት ወደ መቶኛ ያልተቀየረላቸው እንዲሁም ወደ መቶኛ ሲቀየር በነጥብ ቤት የነበሩ ቁጥሮች ያልተደመረላቸው ተማሪዎች እንደተስተካከለላቸውም አስታውቋል።
በተጨማሪም 49.5 እና በላይ አማካይ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች ውጤታቸው ወደ 50 በመቶ እንዲጠጋጋ በተወሰነው መሠረት ተግባራዊ ተደርጓል ብሏል ተቋሙ፡፡