ሸገር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩትን በዛሬው ዕለት ሥራ ያስጀመሩት የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ፤ በክልሉ የትምህርት ጥራት እና ተደራሽነትን ለማረጋገጥ በትኩረት እየተሠራ መሆኑን ገልጸዋል።
በዛሬው ዕለት ሥራ የጀመረው ሸገር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩትም በዘርፉ የሚስተዋለውን የተደራሽነት ችግር በማቃለል በኩል ጉልህ አስተዋፅዖ እንደሚያበረክት ተናግረዋል።
ኢንስቲትዩቱ በዛሬው ዕለት ተማሪዎችን በመቀበል በይፋ ሥራ መጀመሩን ያስታወቁት የኦሮሚያ ክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ቶላ በሪሶ (ዶ/ር) በበኩላቸው፥ ተቋሙ በክህሎት የታነጹ ብቁ ዜጎችን ለማፍራት ያስችላል ብለዋል።
በኢንስቲትዩቱ ሥራ ማስጀመሪያ መርሐ ግብር ላይ የጨፌ ኦሮሚያ አፈ ጉባዔ ሰዓዳ አብዱራህማን፣ የሸገር ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ተሾመ አዱኛ (ዶ/ር)፣ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች እና አባ ገዳዎች ተገኝተዋል።
#ebcdotstream #oromia #sheger #education #institute