Search

እንደ ስሙ ተዓምር እየሠራ ያለው ራጂ አሸናፊ

ቅዳሜ ጥቅምት 08, 2018 1630

ራጂየሚለው ቃል የአፋን ኦሮሞ ቃል ሲሆን ትርጉሙ ተዓምር ማለት ነው።ስምን መልአክ ያወጣዋል” እንዲሉ ታዲያ በዚህ ቃል የተሰየመው ራጂ አሸናፊ በፊዚክስ ተዓምር እየሠራ ይገኛል።

ራጂ ተወልዶ ያደገው ከአዲስ አበባ 700 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘውቄለም ወለጋዋ ጊዳሚ ነው። የስምንተኛ ክፍል ውጤቱ ከፍተኛ ስለነበር የኦሮሚያ ልማት ማኅበር በሚያስተዳደረው ኦዳ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት የመማር ዕድል አግኝቷል።

ለቤተሰቡ ዘጠነኛ ልጅ የሆነው ራጂ በቤተሰቡ ውስጥ ትምህርት እንደ ምርጫ ሳይሆን እንደ ሕይወት መመሪያ ስለሆነ ሁሉም የቤተሰቡ አባላት መማራቸውን ተናግሯል።

ኦዳ ካስፈተናቸው የመጀመሪያዎቹ 12 ክፍል ተማሪዎች መካከል የሆነው ራጂ፤ በሀገር አቀፍ ደረጃ ሁለተኛውን ከፍተኛ ውጤት (647) በማስመዝገብ አዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲን ተቀላቀለ።

ከአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ (ASTU) አፕላይድ ፊዚክስእና በ‘አፕላይድ ሂሳብከፍተኛ ውጤት በማስመዝገብ 2014 . በሁለት ዲግሪዎች ተመርቋል።

በዩኒቨርሲቲው ቆይታው 60 የትምህርት ዓይነቶች A+ ያገኘ የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ ተማሪ በመሆን ዕውቅና አግኝቷል።

ባስመዘገበው ከፍተኛ ውጤትም በዓለም አቀፍ ደረጃ ታዋቂ ከሆነው የማሳቹሴትስ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት (MIT) የድኅረ ምረቃ ትምህርት ዕድል አግኝቷል።

በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የመጀመሪያ ዲግሪውን ሲማር ባሳየው ልዩ የአካዳሚክ ብቃት ቀጥታ የዶክትሬት ዲግሪ ትምህርት ዕድል ያገኘው ራጂ፤ በሦስተኛ ዲግሪ ትምህርቱም ከፍ ያለው ዕውቅናው ቀጥሏል።

ራጂ አሁን በማሳቹሴትስ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት እየተማረ ያለው ኢነርጂ ፊዚክስአካል የሆነውንቲዎሬቲካል ፊዚክስሲሆን፤ ለትምህርቱ ልዩ ፍቅር እንዳለው ይገልጻል።

በቲዎሬቲካል ፊዚክስ መስክ የምርምር ጽሑፎችን ከአሜካሪው ፕሮፌሰር ባርተን ዝዊባች ጋር በጋራ አሳትሟል፤ እነዚህም፥ "Type II RR string fields and exotic diffeomorphisms" "Boundary terms in string field theory" እና "Gauge algebra and diffeomorphisms in string field theory" የሚሉ ናቸው።

በማሳቹሴትስ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት (MIT) ትምህርቱን ከመጀመሩ በፊት በጣሊያን፣ ትሪስቴ በሚገኘው አብዱስሰላም ኢንተርናሽናል ቲዎሬቲካል ፊዚክስ ማዕከል (ICTP) የአንድ ዓመት ኮርሶችን ወስዷል።

2023 ከዚሁ ተቋም (ICTP) በከፍተኛ ኢነርጂ፣ ኮስሞሎጂ እና አስትሮፓርቲክል ፊዚክስ የተሰጡትን ኮርሶች ሲያጠናቅቅ በዘርፉ ካሉት ከፍተኛ ምሁራንአንዱን እውቅና ያገኘበትን ውጤት በማስመዝገብ ነበር።

ራጂ የወደፊት ራዕዩን ሲገልጽም፥ ቲዎሬቲካል ፊዚክስሊቅ ሆኖ ወደ ኢትዮጵያ በመመለስ በኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎች የቲዎሬቲካል ፊዚክስ ማዕከላትን ማቋቋም እና ለተማሪዎች ዕድል መፍጠር መሆኑን ይናገራል።

ወጣቱ ኒውዮርክ በሚገኘው የተመድ ዋና መሥሪያ ቤት በተካሄደው ዓለም አቀፍ የንድፈ ሃሳባዊ ፊዚክስ መድረክ ላይ ተገኝቶ የወደፊት ራዕዩን አጋርቷል። 

ራጂ በመድረኩ ላይ ከትውልድ ሀገሩ ከኢትዮጵያ እስከ ማሳቹሴትስ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ያደረገውን ጉዞ እና የገጠሙትን ውጣ ውረዶች ዘርዝሯል።

በኢንስቲትዩቱ የሚገኙ መምህራኑ ቀጣዮቹን የዓለም የሳይንስ ሊቃውንት እንደሚያፈሩ እምነት እንዳለው እና እሱም ይህን ዕድል በማግኘቱ ደስተኛ መሆኑን ገልጿል።

ባደገበት አካባቢ ባሉ ትምህርት ቤቶች ሌላው ቀርቶ በቂ ወንበሮች እና ጠረጴዛዎች እንዳልነበሩ የሚጠቅሰው ራጂ፤ ዩኒቨርሲቲ እስከሚገባ ድረስ ኮምፒዩተር አግኝቶ እንደማያውቅ ተናግሯል።

የተፈጥሮ ሳይንስ ፈጣን ውጤት ስለማያሳይ እና ከባድም ስለሆነ ብዙዎች እንደማይመርጡት ገልጾ፤ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን ሊያናቀቅ ወደ መጨረሻው ሲደርስ ስለኳንተም ፊዚክስሰምቶ በፍቅሩ መውደቁን ገልጿል።

በኢትዮጵያ ውስጥ ቲዎሬቲካል ፊዚክስ የሚያስተምሩ ዩኒቨርሲቲዎች ስለሌሉ አፕላይድ ፊዝክስ ለመማር መወሰኑን ያወሳው ራጂ፤ በዚያም በርካታ ውጣ ውረዶች ቢኖሩም ዓላማው ላይ አተኩሮ መሥራቱን ተናግሯል።

አሁን ባለበት ማሳቹሴትስ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ከዓለም ዙሪያ ከመጡ ተማሪዎች ጋር ያለው ፉክክር ከባድ ቢሆንም በትምህርቱ ደስተኛ መሆኑን እና ከሁሉም በላይ መምህራኑ በተማሪዎቻቸው ላይ ያላቸው እምነት ብርታት እንደሆነው አንስቷል።

ባደጉ ሀገራት ያሉ ተማሪዎች መሰረታዊ ሳይንስን ከታች ጀምረው እየተማሩ ስለሚመጡ በኢንስቲትዩቱ ያላቸው ብቃት እና ፉክክርም የላቀ እንደሆነ እና በኢትዮጵያም እንደዚህ ዓይነቱ ባህል መለመድ እንዳለበት ጠቁሟል።

በማሳቹሴት ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ሦስተኛ ዲግሪ እየሠራ ያለ ብቸኛው ጥቁር እንደሆነ የጠቀሰው ራጂ፤ በዓለም ላይ በርካታ ልዩ ተሰጥዖ ያላቸው ተማሪዎች ስላሉ ዕድሉን ቢያገኙ ዓለም የነገዎቹን ምርጥ ሳይንቲስቶች ልታገኝ እንደምትችል ተናግሯል።

ራጂ በግሉ በተለያዩ አጋጣሚዎች ባደረጋቸው ቃለመጠይቆች ወደኋላ ስለሚጎትቱት ችግሮች ማሰብ እንደማይፈልግ እና ከችግሮች ውስጥ ዕድሎችን ለማግኘት እንደሚጥር ተናግሯል።

በለሚ ታደሰ

#ebcdotstream #RajiAshenafi #ASTU #ICTP #MIT #USA #Massachusetts #TheoreticalPhysics