ሸገር ከተማ በ2015 ዓ.ም በአዲስ እና በሙሉ ሐሳብ የተደራጀች ሲሆን፤ በአሁኑ ወቅት ከተማዋን የማዘመን ሥራ በስፋት እየተከናወነ ይገኛል።
በከተማዋ የልማት ሥራዎች ከተለመደው የሥራ ሰዓት ባሻገር በምሽትም በስፋት በመከናወን ላይ ይገኛሉ።
ሸገር ከተማ በርካታ ኢንዱስትሪዎች የሚገኙባት እንደመሆኗ፤ ከፍተኛ ኢኮኖሚ በማንቀሳቀስ ላይ ትገኛለች።
በከተማዋ የቱሪስት መዳረሻ የሆኑ ባህላዊ መስህቦች እንዲሁም የሆቴል እና መስተንግዶ አገልግሎቶች በስፋት እየለሙ ነው።
የኢቲቪ ቅዳሜ አመሻሽ ፕሮግራም የሸገር ከተማ የኮሪደር ልማት እንቅስቃሴ እና የምሽት ድባብን ቅኝት አድርጓል።

ሸገር ከተማ በሚቀጥሉት 10 እና 15 ዓመታት ውስጥ በአፍሪካ ምርጥ ከሚባሉ ከተሞች አንዷ እንድትሆን ራዕይ ሰንቆ በመሥራት ላይ እንደሚገኝ የሸገር ከተማ አስተዳደር ገልጿል።
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲን ጨምሮ ከተለያዩ ተቋማት ጋር የከተማዋን ማስተር ፕላን በማጥናት እየተከናወኑ ያሉ ሥራዎች መኖራቸውን ከኢቲቪ ጋር ባደረጉት ቆይታ የከተማዋ አመራሮች ተናግረዋል።
በከተማ ደረጃ ከ8 በላይ የልማት ኮሪደሮች መኖራቸውን የጠቀሱት አመራሮቹ፤ ይህም ከሌሎች ከተሞች ለየት እንደሚደርጋት ገልጸዋል።
የልማት ኮሪደሮቹ የፋይናንሻል ማዕከል፣ የኢንዱስትሪ ማዕከል፣ የሎጂስቲክስ ማዕከል፣ ዓለም አቀፍ የትምህርት ተቋማት እንዲሁም የአረንጓዴያማ አካባቢዎች ማዕከልን እንደሚያካትቱ ዘርዝረዋል።
የከተማዋን መሠረተ ልማት በመዘርጋት እና የአገልግሎት አሰጣጧን በማዘመን ከተማዋን የኢንቨስትመንት መዳረሻ ለማድረግ እየተሠራ ስለመሆኑም አመራሮቹ አብራርተዋል።
በጥቅሉ ሸገር ከተማ በሚቀጥሉት ጥቂት ዓመታት በአፍሪካ ካሉ ምርጥ 20 ከተሞች መካከል አንደኛዋ እንድትሆን ታሳቢ ያደረጉ ሥራዎች በመከናወን ላይ ናቸው ነው ያሉት።
በንፍታሌም እንግዳወርቅ
#etv #ebcdotstream #ethiopia #oromia #shegercity #africa