Search

የመዲናዋ ስፖርት ማዕከላት የነዋሪዎችን ስፖርታዊ እንቅስቃሴ እያጎለበቱ ነው - ከንቲባ አዳነች አቤቤ

እሑድ ጥቅምት 02, 2018 151

በአዲስ አበባ የተገነቡ የስፖርት ማዕከላት ነዋሪዎች ስፖርታዊ እንቅስቃሴን ባህል፣ የአኗኗር ዘይቤ፣ ጤናን መጠበቂያ፣ ማህበራዊ ግንኙነትን ማጎልበቻ መንገድ እንዲያደርጉ አስችለዋል ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ።

ከንቲባ አዳነች በማኅበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ፥ በየዕለቱ በተለይም በረፍት ቀናት ህፃናት፣ ወጣቶች፣ አረጋውያን በተናጠል እና በጋራ የተለያዩ ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎችን በመኖሪያ አካባቢ እና ለትራፊክ እንቅስቃሴ ዝግ በሆኑ መንገዶች ሲያከናውኑ ስለመመልከታቸው ጠቅሰዋል።

ይህም ጤናን ለመጠበቅ፣ ተተኪ ስፖርተኞችን ለማፍራት የሚያግዝ በመሆኑ ህብረተሰቡ ወደ ማዕከላቱ በመሄድ ስፖርታዊ እንቅስቃሴ የማድረግ ልምምዱን ይበልጡን ማሳደግ ይገባዋል ሲሉ ገልጸዋል።

#ebcdotstream #addisababa #masssport