የሶማሊ ክልል ርዕሰ መዲና በሆነችው ጅግጅጋ በአራቱም አቅጣጫ ተደራሽ የሆነው የኮሪደር ልማት ከተማዋ ከዘመኑ የክልል ከተሞች ተርታ እንድትሰለፍ ያስቻለ ነው ሲሉ የጅግጅጋ ከንቲባ ሻፊ አክመድ (ኢ/ር) ገልጸዋል።
ከ12 ሺህ በላይ ለሆኑ ዜጎች የሥራ ዕድል በፈጠረው የጅግጅጋ የመጀመሪያ ዙር የኮሪደር ልማት በጥቅሉ 10 ኪሎ ሜትር መንገድ የተገነባ ሲሆን፤ በሁለተኛው ዙር የኮሪደር ልማት ደግሞ 20 ኪሎ ሜትር መንገድ ለመገንባት ስለመታቀዱ ነው ከንቲባ ሻፊ ከኢቢሲ ጋር ባደረጉት ቆይታ የገለጹት።
ይህም ደረጃቸውን የጠበቁ ዋና መንገዶች እንዲገነቡ ብሎም የዜጎች የአኗኗር ዘይቤ እንዲሻሻል ስለማስቻሉ ከንቲባው ተናግረዋል።
በሌላ በኩል ከተማዋ በኮሪደር ልማቱ የተጎናጸፈችውን ውብ ገጽታ በማስጠበቅ ለኢንቨስተሮች የተለያዩ አማራጮች ስለመዘጋጀታቸው ከንቲባ ሻፊ አንስተዋል።
አክለውም፥ በከተማዋ እየተከናወነ ባለው ልማት በእጅጉ የተነቃቃችው ጅግጅጋ በመጪዎቹ ዓመታት ከሀገሪቱ ዋና ዋና ከተሞች ጋር የሚገዳደር ደረጃ ላይ እንደምትደርስ ያላቸውን እምነት ገልጸዋል።
በአፎሚያ ክበበው
#ebcdotstream #corridordevelopment #urbancorridor #jigjiga