የብልፅግና ፓርቲ አመራሮች በአዲስ አበባ የልማት ሥራዎች ጉብኝት እያደረጉ ይገኛሉ።
በኢሬቻ ፓርክ እየተደረገ ባለው በዚህ ጉብኝት በከተማዋ ተግባራዊ እየተደረጉ ያሉ ሰው ተኮር ፕሮጀክቶችን ተመልክተዋል።
የዜጎችን የቤት ጥያቄ ለመመለስ የተለያዩ የቤት ልማት አማራጮችን በመከተል ማለትም በመንግሥት ብድር፣ በበጎ ፈቃድ፣ በከተማ አስተዳደሩ በጀት፣ በግል ባለሀብቶች ብሎም በግል እና በማኅበር ተደራጅተው ቤቶች እንዲለሙ በማስቻል የዜጎችን የቤት ጥያቄ ለመመለስ እየተሠራ መሆኑን በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ ኃላፊ ጀማሉ ጀንበር (ዶ/ር) ገልጸዋል።
እነዚህ የቤት ልማት ሥራዎች የቤት ጥያቄዎችን ከመመለስ ባሻገር ለዜጎች ማኅበራዊ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችሉ ሆነው መሠራታቸውን ገልጸዋል።
በብልፅግና እሳቤ የተቃኘ የገበያ ሥርዓት በመዘርጋት የምርት እና አቅርቦት ማዕከላት እየለሙ መሆኑም ተገልጿል።
እነዚህም የደላላን ሰንሰለትን በመበጠስ ዜጎች ከገበሬው በቀጥታ ምርት እንዲያገኙ ማስቻላቸው ነው ተብሏል። ይህም የኑሮው ውድነትን በመቀነስ ረገድ ጉልህ ሚናን እየተጫወቱ ነው።
በብሩክታዊት ተገኝ
#EBC #ebcdotstream #AddisAbaba #Prosperityparty