Search

ለሀገር ሁለንተናዊ እድገት ቁልፍ ሚና ያላቸው አካታች የልማት ስራዎች

ቅዳሜ ጥቅምት 29, 2018 37

ለሀገር እድገት እና ከፍታ ሁሉንም አሳታፊ ያደረገ ልማት መገንባት እንደሚገባ ይገለጻል፡፡

የፕሮ ካፒታል ፒኤልሲ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ተስፋዬ ምግባር፤ በሀገሪቱ የሚከናወኑ ማንኛውም የልማት ስራዎች ሁሉንም ያካተቱ መሆን እንደሚገባቸው ከኤፍ ኤም አዲስ 97.1 ጋር በነበራቸው ቆይታ ተናግረዋል፡፡

አካታች እና ዘላቂ ልማት ለማረጋገጥ መንግሥት የጀመራቸውን ስራዎች አጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባው አክለዋል፡፡

በገጠር እና በከተማ ያለውን ኢኮኖሚያዊ ትስስር ማጠናከር እንደሚገባም ነው የገለጹት፡፡

በከተማ የሚከናወኑ የመሰረተ ልማቶች ስራዎችን በገጠሩም በመተግበር ያለውን ልዩነት ማጥበብ እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል፡፡

በገጠር ላሉ ወጣቶች የተሻለ የስራ እድል በመፍጠርና በገበያ ተወዳዳሪ በማድረግ ወደ ከተማ የሚደረጉ ፍልሰቶችን ማስቀረት እንደሚቻልም ነው የጠቀሱት፡፡

ከዚህ ጋር በተገናኘም አካል ጉዳተኞችን እና አቅመ ደካማዎችን መደገፍ እንደሚገባ አክለዋል፡፡

አካታች ልማት ለወጣቱ የስራ እድልን እንደሚፈጥር እና ለሀገር የኢኮኖሚ እድገት አስተዋጽኦ እንደሚኖረውም ተናግረዋል፡፡

መሰረተ ልማቶች ሲሟሉ ለቀጥተኛ ኢንቨስትመንት ምቹ እንደሚሆኑም ነው የጠቆሙት፡፡

በሜሮን ንብረት

#ebc #ebcdotstream #Ethiopia #Inclusivedevelopment