Search

በፋሲል አብያተ-መንግሥት ላይ የተሠራው ሥራ እድሳት ብቻ ሳይሆን ታሪክን የማስቀጠል ትልቅ ሥራ ነው፦ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

ቅዳሜ ጥቅምት 29, 2018 134

በፋሲል አብያተ-መንግሥት ላይ የተሠራው ሥራ ዝም ብሎ እድሳት ብቻ ሳይሆን ታሪክን የማስቀጠል ትልቅ ሥራ ነው ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ።

ኢትዮጵያ ትልቅ እና ረዥም የሀገረ መንግሥት ታሪክ ያላት ሀገር መሆኗን አንስተው፤ የዚህ መገለጫ የሆኑ በርካታ አብያተ-መንግሥት ሰሜን ኢትዮጵያን ጨምሮ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች እንደሚገኙ አክለዋል።

የፋሲል አብያተ-መንግሥት ከኢትዮጵያ አልፎ የዓለም ቅርስ መሆናቸውን ጠቅሰው፤ ቅርሶቹ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (/) ሀሳብ አመንጪነት ታሪካዊነታቸውን በጠበቀ መልኩ ታድሰው ተጠብቀው ለትውልድ እንዲቆዩ መደረጉን ጠቅሰዋል።

በቅርሶቹ የእድሳት ሂደት ከጅምሩ አንስቶ ከውስጥም ከውጭም ጫናዎች እንደነበሩ አስታውሰው፤ ጫናዎቹን  በመቋቋም እድሳቱን "አብያተ-መንግሥቱ እንደ አዲስ ተሠሩ፤ ዳግም ተወለዱ" በሚያስብል ደረጃ በአጭር ጊዜ ማጠናቀቅ መቻሉን ተናግረዋል።

በቅርሶቹ ላይ የተሠራው ሥራ እድሳት ብቻ ሳይሆን ታሪክን የማስቀጠል ትልቅ ሥራ ነው፤ ሥራው ኢትዮጵያ ታላቅ ሀገር እንደነበረች እና እንደምትሆን የሚያሳይ ምልክት ሆኗል ብለዋል።

ኢትዮጵያ መሥራት እንደምትችል እና የሚያቅታት ምንም ነገር እንደሌለ በተግባር እያሳየች ነው ሲሉም ገልጸዋል።

በሜሮን ንብረት

#EBCdotstream #Gondar #Fasil