የሶማሊ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ ሙሁመድ በክልሉ ርዕሰ መዲና ጅግጅጋ ከተማ የዘመናዊ ድልድይ ግንባታን አስጀምረዋል።
በዘመናዊ መልኩ እንደሚገነባ የተነገረለት ድልድዩ የተሽከርካሪ፣ የእግረኛ እና የብስክሌት መንገዶችን ያካተተ መሆኑን ተገልጿል።
የ36 ሜትር ስፋት ያለው ድልድዩ ትልልቅም፣ አነስተኛም ተሽከርካሪዎችን በአግባቡ ማስተናገድ እንደሚችልም ነው የተገለጸው።
ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፋ ሙሁመድ፥ የክልሉ መንግሥት የጅግጅጋ ከተማን ለንግድ እና ኢንቨስትመንት ተመራጭ ለማድረግ በርካታ ተግባራትን ማከናወኑን ተናግረዋል።
በጅግጅጋ ከተማ እየተከናወነ የሚገኘው የኮሪደር ልማት ሥራ የከተማዋን ነዋሪ እና የትራንስፖርቱን እንቅስቃሴ በማቀላጠፍ ጊዜን ለመቆጠብ ማስቻሉን ገልጸዋል።
ዛሬ ግንባታው የተጀመረው ድልድይ ሥራው ሲጠናቀቅ በሰዎች እና በተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴ ላይ የራሱ በጎ ተፅዕኖ እንደሚኖረውም ነው የተናገሩት።
መንግሥት ጅግጅጋን ጨምሮ በክልሉ የሚገኙ ከተሞችን ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ የሚያፋጥኑ የመሠረተ ልማት ግንባታዎችን በመፍጠር እና መፍጠን እሳቤ ለማከናወን መዘጋጀቱንም ርዕሰ መስተዳድሩ አረጋግጠዋል።
በቴዎድሮስ ታደሰ
#ebcdotstream #ethiopia #urbancorridor #jigjiga #bridg