Search

320 የታካሚዎች አልጋ የያዘው የዘውዲቱ ሆስፒታል ማስፋፊያ ሥራ ጀምሯል:- ከንቲባ አዳነች አቤቤ

ቅዳሜ ኅዳር 06, 2018 84

ዛሬ በአንጋፋው የዘውዲቱ መታሰቢያ ሆስፒታል አዲስ ሆስፒታልን የሚመጣጠን ማስፋፊያ ገንብተን፤ ዘመናዊ የሕክምና መሳሪያ አሟልተን ሥራ አስጀምረናል ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለፁ።
በዘውዲቱ መታሰቢያ ሆስፒታል የተገነባው የላቀ የሕክምና ማዕከል፣ በ1 ሺህ 800 ካ.ሜ ስፋት ላይ ያረፈ እና ባለ 10 ወለል ሕንፃ ሲሆን ለተኝቶ ታካሚዎች አገልግሎት የሚሰጥ 320 አልጋ እንዳለው ተገልጿል።
ይህም ላለፉት 91 ዓመታት የነበረውን የዘውዲቱ ሆስፒታል ታካሚ አገልግሎትን በእጥፍ ያሳድገዋል ሲሉ ከንቲባዋ ጠቁመዋል።
 
ሆስፒታሉ ለሕክምና ባለሙያው እና ለታካሚው በሚመች መልኩ የተገነባ ሲሆን አሁን ላይ የህክምናው ዘርፍ በደረሰበት ዘመናዊ የህክምና መሳሪያዎች የተደራጀ እና የራሱ ኦክስጂን ማምረቻ ጭምር ያለው ነው ብለዋል።
ይህ ሆስፒታል አስተዳደራችን አዲስ አበባን የሜዲካል ቱሪዝም ማዕከል ለማድረግ ለጀመረው ሥራ ተደማሪ አቅም የሚፈጥር ይሆናል ሲሉ ገልጸዋል።