ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ የደሴ ከተማ መሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት በይፋ አስጀምረዋል፡፡
በማስጀመርያ መርኃ ግብሩ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ መንግስት ሕዝቡ ከመንግሥት ማግኘት የሚገባውን አገልግሎት በተገቢው እና በሠለጠነ መልኩ ማግኘት አለበት ብሎ ያምናል ብለዋል፡፡
ዛሬ ከ120 ዓመት በላይ ያስቆጠረቸው ደሴ የብልጽግና ወጋገን ፈንጥቃለች በማለትም ለነዋሪዎቿ ምቹ የሆነች የበለጸገች እና የተዋበች ከተማ ወደመሆን የሚያስጉዛትን የተስፋ ጎዳና ተያይዛለች ሲሉ ተናግረዋል።
ተገልጋዮች ጊዜያቸውን፣ ገንዘባቸውን እና ጉልበታቸውን በአግባቡ እንዲጠቀሙ በማድረግ ረገድ መሶብ ፋይዳው የላቀ ስለመሆኑና አገልግሎቱ በሕዝብ እና በመንግሥት መካከል ያለውን ጥብቅ ቁርኝት ወደተሻለ ደረጃ የሚያሳድግ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡
በመሆኑም ይህንን የአንድ ማዕከል አገልግሎት የበለጠ ማጠናከርና ማስፋፋት ይገባል ሲሉ ነው ያሳሰቡት፡፡
በ290 ሚሊዮን ብር በሁለት ወራት ውስጥ ተጠናቆ ለአገልግሎት ዝግጁ የሆነው መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት የአካባቢው ነዋሪዎች የአገልግሎት አሰጣጥ ችግር ቅሬታ የሚፈታ ነው ተብሏል፡፡
በአሸናፊ እንዳለ
#Ebc #Ebcdotstream #Ethiopia #Dessie #Mesob