Search

መንግሥት ዜጎችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ሥራዎችን አጠናክሮ ይቀጥላል - ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

እሑድ ኅዳር 07, 2018 123

መንግሥት ዜጎችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ሥራዎችን አጠናክሮ ይቀጥላል ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ተናገሩ።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በኮምቦልቻ ከተማ ቦርከና ክፍለ ከተማ ውስጥ ለአቅመ ደካሞች እና አረጋውያን የተገነባውን አብሮነት የጋራ መኖሪያ ጎብኝተዋል።
ባለፉት ዓመታት መንግሥት ለሰው ተኮር ፕሮጀክቶች ልዩ ትኩረት ሰጥቷል ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን፤ በከተማዋ የተከናወነውን ሥራም አድንቀዋል።
36 አባዎራዎችን ተጠቃሚ ያደረገው የጋራ መኖሪያው 42 ሚሊዮን ብር ወጪ የተደረገበት ሲሆን፤ በከተማ አስተዳደሩ፣ በባለሀብቶች እና በማህበረሰቡ ትብብር የተገነባ ነው።
በተያያዘም ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር የዲጂታላይዜሽን የሥራ ሂደትን ተመልከተዋል።
በአሸናፊ እንዳለ