Search

ኢትዮጵያ የተሳተፈችበት የብሪክስ ማዕከላዊ ባንኮች የሳይበር ደህንነት ሴሚናር

ማክሰኞ ኅዳር 09, 2018 112

ኢትዮጵያ በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ማዕከላዊ ባንክ አዘጋጅነት በተካሄደው የብሪክስ ማዕከላዊ ባንኮች የሳይበር ደህንነት ሴሚናር ላይ ተሳትፋለች።

የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ማዕከላዊ ባንክ (ሲቢዩኤኢ) የሳይበር ደህንነት ሴሚናርን እና ለብሪክስ ማዕከላዊ ባንኮች ደግሞ ሁለተኛውን የሳይበር ደህንነት ሴሚናር አስተናግዷል።

በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ማዕከላዊ ባንክ (ሲቢዩኤኢ) የተዘጋጀው ይህ የሁለት ቀናት ሴሚናር፤ ዓለም አቀፍ የሳይበር ጥበቃን ለማጠናከር እና የፋይናንስ መረጋጋትን ለማስጠበቅ ያለመ ነው ተብሏል።

በመድረኩ ከብሪክስ ማዕከላዊ ባንኮች የተውጣጡ ባለሙያዎች በተራቀቁ ቴክኖሎጂዎች ሳቢያ ስለሚመጡ የወደፊት የሳይበር ስጋቶች ዙሪያ ተወያይተዋል።

ውይይቱም አቅማቸውን እንዲገመግሙ፣ ማሻሻያዎችን ለማድረግ የሚያስችሉ ቦታዎችን እንዲለዩ እንዲሁም የዓለም አቀፉን የፋይናንስ መሠረተ ልማት አቅም ለማሳደግ የሚረዱ ውጤታማ ቴክኒኮችን በተመለከተ ልምዶቻቸውን እንዲያካፍሉ ማስቻሉ ተገልጿል።

በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ማዕከላዊ ባንክ የገንዘብ ፖሊሲ እና የፋይናንስ መረጋጋት ረዳት ገዥ የሆኑት ኢብራሂም ኦቤይድ አል ዛቢ፤ "እያደገ ያለው የቴክኖሎጂ እና የሳይበር ጥቃት የጋራ እና ቅድመ ጥንቃቄ የተሞላበት የመከላከያ ስትራቴጂን ይጠይቃል" ብለዋል።

በሴራን ታደሰ

#Ebc #Ebcdotstream #Ethiopia #BRICS #Cybersecurity