የማሌዢያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዳቶ ሰሪ አንዋር ቢን ኢብራሂም በኢትዮጵያ የነበራቸውን የሶስት ቀናት ይፋዊ የሥራ ጉብኝት አጠናቀው ወደሀገራቸው ተመልሰዋል።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ የኢትዮጵያ ጉብኝታቸውን ላጠናቀቁት የሚሌዢያው ጠቅላይ ሚኒስትር እና ልዑካቸው ቡድናቸው በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ተገኝተው አሸኛኘት አድርገዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዳቶ ሴሪ አንዋር ኢብራሂም በኢትዮጵያ ቆይታቸው ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጋር በሁለቱ ሀገራት የሁለትዮሽ ሁለንተናዊ የዲፕሎማሲ ትብብር ዙሪያ መክረዋል።
በኢትዮጵያና ማሌዢያ መካከል በቱሪዝም፣ በጤና፣ የአየር ትራንስፖርት አገልግሎት እና በሌሎች ዘርፎች በትብብር ለመስራት የሚያስችሉ ስምምነቶችንም ተፈርመዋል።
የማሌዥያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዳቶ ሴሪ አንዋር ኢብራሂም በኢትዮጵያ ቆይታቸው የተለያዩ ተቋማትንም ጎብኝተዋል።
የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ታየ አጽቀ ሥላሴ በተገኙበት በአዲስ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል በተካሄደው የኢትዮ-ማሌዢያ ከፍተኛ የቢዝነስ ፎረም ላይም ጠቅላይ ሚኒስትር ዳቶ ሴሪ አንዋር ኢብራሂም ተሳትፈዋል።
ከዚህ ባሻገር በአዲስ አበባ እና ኳላ ላምፑር ከተሞች መካከልም የእህትማማችነት የትብብር መግባቢያ ሰነድ ስምምነትም ተፈርሟል።
በሳምሶን በላይ
#EBC #EBCdotstream #Ethiopia #Malaysia #DiplomaticRelations