Search

ኢትዮጵያውያን ከጥንት ጀምሮ የርኅራኄ፣ የፍትሕ እና የቻይነት መገለጫ ናቸው - የማሌዥያው ጠቅላይ ሚኒስትር ዳቶ ሰሪ አንዋር ቢን ኢብራሂም

ሓሙስ ኅዳር 11, 2018 94

የማሌዥያው ጠቅላይ ሚኒስትር ዳቶ ሰሪ አንዋር ቢን ኢብራሂም፣ የኢትዮጵያ እና የማሌዥያ ወዳጅነት ከተለመደው ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የተሻገረ መሆኑን ገልጸዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በብሔራዊ ቤተመንግሥት በተደረገላቸው የእራት ግብዣ ላይ ባደረጉት ንግግር፣ ኢትዮጵያውያን ከጥንት ጀምሮ የርኅራኄ፣ የፍትሕ እና የቻይነት መገለጫ ናቸው ብለዋል።

በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (/) ላይ ያላቸው እምነት እና መተማመን ከፍተኛ መሆኑንም ገልጸዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባለፈው ዓመት በማሌዥያ ያደረጉትን ጉብኝት በማስታወስም፣ በዚያ ጉብኝታቸው የጥሩ ወዳጅነት ትርጉምን በግልጽ አሳይተዋል ብለዋል።

ኢትዮጵያ የረጅም ታሪክ እና የሥልጣኔ ባለቤት መሆኗን እናውቃለን ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዳቶ ሰሪ አንዋር ቢን ኢብራሂም፣ ይህቺ ታላቅ ሀገር ነቢዩ ሙሐመድ (..) ተከታዮቻቸውን በአደራ የላኩባት ሀገር መሆኗን ዘወትር የማነሣው ጉዳይ ነው ሲሉ ተናግረዋል።

ተከታዮቹ በወቅቱ በንጉሥ አል ነጃሺ የተደረገላቸው እንክብካቤ እና የተሰጣቸው ከለላ ኢትዮጵያውያን ከጥንት ጀምሮ የሐቀኛ ርኅራኄ፣ ፍትሕ እና የቻይነት መገለጫ መሆናቸውን ያሳዩበት ነበር፤ ይህን በአግባቡ እንረዳለን ብለዋል።

በኢትዮጵያ የተጀመረው የ“መደመር” እሳቤ እና ማሌዥያ የምትከተለው የ‘ማዳኒእሳቤ ተመሳሳይነት ያላቸው መሆኑን ገልጸው፣ እነዚህ እሳቤዎች ከቁሳዊ ዕድገት፣ ልማት እና ቢዝነስ ባሻገር በሰብዓዊ ዕድገት እና እሴት ላይ እንደሚያተኩሩ ተናግረዋል።

ሁለቱ ሀገራት በእነዚህ ወሳኝ እሳቤዎች ስለሚመሩ ስለ ዘላቂነት፣ አካታችነት እና ዕድገት ስንናገር ሕዝብን ማዕከል ባደረገ መልኩ ነው ብለዋል።

በኢትዮጵያ ያደረጉት ቆይታ አጭር ቢሆንም እጅግ ፍሬያማ እንደነበር እና ይህም የመልካም ወዳጅነት ፍሬ መሆኑን ገልጸው ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (/) እና ለኢትዮጵያ ምስጋና አቅርበዋል።

በዮናስ በድሉ

#EBC #ebcdotstream #Ethiopia #Malaysia #diplomacy