Search

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) Compact with Africa (CwA) መርኃ ግብር ላይ ተካፈሉ

እሑድ ኅዳር 14, 2018 70

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከቡድን 20 ጉባኤ ጎን በተካሄደው Compact with Africa (CwA) መርኃ ግብር ላይ ተካፍለዋል።

መርኃ ግብሩ ሥራው የደረሰበትን ደረጃ በመገምገም የወደፊት ትልሙን መመልከት ላይ ያተኮረ ነበር።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በንግግራቸው የማክሮ ኢኮኖሚ መረጋጋት ሥራዎችን፣ እንደ ገበያን ክፍት የማድረግ ተግባራት፣ የቁጥጥር ማህቀፎች የማጠናከር ሥራዎች፣ የካፒታል ገበያዎችን የማበርታት እንቅስቃሴዎች ያሉ የኢትዮጵያን ወሳኝ የኢኮኖሚ ሪፎርም ሥራዎችን አንስተው፤ የረጅም ጊዜ የግል ኢንቨስትመንትን በመሳብ የኢትዮጵያን ተወዳዳሪነት ከፍ ለማድረግ እንዳስቻሉ አውስተዋል።

መርኃ ግብሩ Compact with Africa 2.0 የአፍሪካን ብሎም የሰፊውን ዓለም የጋራ ብልጽግና በማሳደግ ረገድ ከፍ ያለ ርዕይ ሊይዝ እንደሚገባ ጥሪ በማስተላለፍ መጠናቀቁን የጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት አስታውቋል።

#Ebc #Ebcdotstream #Ethiopia #PMAbiy #PMOEthiopia #G20Summit