Search

የኢትዮጵያን ሪፎርም ለመደገፍ ቁርጠኞች ነን - ክሪስታሊና ጆርጂዬቫ

እሑድ ኅዳር 14, 2018 80

የዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (አይኤምኤፍ) ለኢትዮጵያ ሪፎርም የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል የድርጅቱ ዋና ዳይሬክተር ክሪስታሊና ጆርጂዬቫ ተናገሩ፡፡

ዋና ዳይሬክተሯ በደቡብ አፍሪካ ከተካሄደው የቡድን 20 የመሪዎች ጉባኤ ጎን ለጎን ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጋር ፍሬያማ ውይይት ማድረጋቸውን በኤክስ ገጻቸው ላይ አስታውቀዋል።

ውይይታቸው ዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት በሚያደርጋቸው የፕሮግራም ድጋፎች በመጡ ለውጦች እና በቀጣይነትም ድጋፉን ሁሉን አቀፍ እና አካታች ማድረግ በሚቻልባቸው ሂደቶች ላይ ያተኮረ እንደሆነ ነው የገለጹት፡፡

አይኤምኤፍ የኢትዮጵያን ልማት ለመደገፍ ቁርጠኛ መሆኑንም ዋና ማኔጂንግ ዳይሬክተሯ አረጋግጠዋል።

በአፍሪካ ምድር ለመጀመሪያ ጊዜ በተካሄደው የቡድን 20 የመሪዎች ስብሰባ ላይ እየተሳተፈች የምትገኘው ኢትዮጵያ ከዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት እና የዓለም ባንክ መሪዎች ጋር ፍሬያማ ውይይቶችን አካሂዳለች፡፡

ከመሪዎቹ ጋር ውይይት ያደረጉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የኢትዮጵያ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ አመርቂ ውጤት እያስመዘገበ መሆኑን ገልጸውላቸዋል።

ከአፍሪካ ልማት ባንክ ፕሬዝዳንት ጋርም ኢትዮጵያ ስለጀመረቻቸው ግዙፍ ፕሮጀክቶች እና የቢሾፍቱ አውሮፕላን ማረፊያን በተመለከተ ስኬታማ ውይይት መደረጉ ተጠቅሷል።

በለሚ ታደሰ

#Ebc #Ebcdotstream #Ethiopia #PMAbiy #G20Summit #IM