Search

የቤት አቅርቦትን ለመጨመር በግሉ ዘርፍ የሚደረጉ ጥረቶችን ማበረታታት አስፈላጊ ነው - ከንቲባ አዳነች አቤቤ ********

እሑድ ኅዳር 28, 2018 45

የቤት አቅርቦትን ለመጨመር በግሉ ዘርፍ የሚደረጉ ጥረቶችን ማበረታታት አስፈላጊ ነው፤ ዛሬ ፊሶን ሪል እስቴት እየገነባቸው ያሉትን 1 ሺ ቤቶችን ተዘዋውረን ተመልክተናል ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ።
እየተገነቡ ያሉት ቤቶች የከተማችንን ደረጃ ለማሻሻል የምንተገብረውን የግንባታ ስታንዳርድ የሚያሟሉ፣ ጥራታቸዉን የጠበቁ መሆናቸውን በጉብኝታችን አይተናል ብለዋል።
ይህ ደግሞ ለኮፕ 32 ተሳታፊዎች አገልግሎት ለመስጠት ተጨማሪ አቅም የሚፈጥር ነው ሲሉ ገልጸዋል።
 
በዘርፉ የተሰማራችሁ የከተማችን አልሚዎች፣ እየገነባችሁ ያላችሁና ለኮፕ 32 እያደረጋችሁ ያለውን አጠቃላይ ቅድመ ዝግጅት በየክፍለ ከተማችሁ ብታሳውቁ የበለጠ ተቀራርቦ ለመስራት እና ጉባኤዉንም የበለጠ ዉጤታማ ለማድረግ ያግዛል ብለዋል።
ለጉባኤው ወደ አገራችን የሚመጡ እንግዶቻችንን በትብብር ለማስተናገድ እና ለጉባኤዉ ዉጤታማነት በጋራ እንስራ ፣ ከወዲሁ እንዘጋጅ በማለት ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለአልሚዎች ጥሪ አቅርበዋል።