በመደመር መንግሥት ከ8 ወራት በፊት በ12 ተቋማት እና 41 አገልግሎቶች የተጀመረው መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት አሁን ላይ 23 ተቅማት እና 180 አገልግሎቶችን ማካተቱን የመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ዳይሬክተር ጄነራል አቶ ጠናህ ማሞ ለኢቲቪ ዜና ተናግረዋል።
በፌደራል ደረጃ ፋይዳ መታወቂያ፣ ፓስፖርት፣ ውክልና፣ ንግድ ፈቃድ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥርን ጨምሮ ከ180 የማያንሱ አገልግሎቶች በአንድ ማዕከል እየተሰጡ መሆኑን ገልጸው፤ አገልግሎቱ ወደ 24 የክልል እና የከተማ አስተዳደር ቅርንጫፎች መስፋቱን አቶ ጠናህ ተናግረዋል።
በሚቀጥሉት 5 ዓመታት በሁሉም ክልሎች እና የከተማ አስተዳደሮች ከ350 እስከ 400 የሚደርሱ መሰል ማዕከላትን በመገንባት ሁሉንም መንግሥታዊ አገልግሎቶች በመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ለመስጠት ርብርብ እየተደረገ መሆኑን አክለው ገልጸዋል።
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ሀብት ቢሮ ኃላፊ ጀማሉ ጀምበር (ዶ/ር) በበኩላቸው፥ አዲስ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት በመዲናዋ በተበታተነ መልኩ ይሰጡ የነበሩ አገልግሎቶችን በተቀናጀ መንገድ በፍጥነት፣ በጥራት እና ፍትሐዊ በሆነ መልኩ ለመስጠት ማስቻሉን ተናግረዋል።
በላሉ ኢታላ
#EBC #ebcdotstream #Ethiopia #Mesob #One-StopServiceCenter