Search

የአልማዝ ኢዮቤልዩውን ምክንያት በማድረግ ነፃ የሕክምና አገልግሎት እየሰጠ ያለው አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ

ሓሙስ ታኅሣሥ 16, 2018 273

75ኛ ዓመት የአልማዝ ኢዮቤልዩ ክብረ በዓሉን በተለያዩ ዝግጅቶች እያከበረ የሚገኘው አንጋፋው አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ይህንኑ ምክንያት በማድረግ ለሠራተኞቹ ለሁለት ቀናት የሚቆይ ነፃ የሕክምና አገልግሎት መስጠት ጀምሯል።

አገልግሎቱ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ እና በጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል  የሕክምና ባለሙያዎች የሚሰጥ ነው።

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ዶ/ር አብዱረዛቅ አህመድ እንዳሉት፥ ነፃ የሕክምና አገልግሎቱ እየተሰጠ ያለው የዩኒቨርሲቲው ሠራተኞች ጤንነታቸውን እንዲያውቁ እና የጤና ዕክል ያለባቸው ደግሞ የሕክምና አገልግሎት እንዲያገኙ ለማገዝ ነው።

በተጨማሪም የዩኒቨርሲቲው የጤና ባለሙያዎች በየወደቁትን አንሱ የነዳያን የበጎ አድራጎት ማኅበር ተገኝተው ነፃ የሕክምና አገልግሎት እንደሚሰጡም ዶ/ር አብዱረዛቅ ተናግረዋል።

የደም ልገሳን ጭምር ያካተተው እና ለሁለት ቀናት የሚቆየው ነፃ የሕክምና አገልግሎት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ስድስት ኪሎ ካምፓስ እና በየወደቁትን አንሱ የነዳያን የበጎ አድራጎት ማህበር እንደሚሰጥ ተገልጿል።

በሰናይት ሰይፉ

#EBC #ebcdotstream #AAU #75years #anniversary #silverjubilee #communityservice