የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እና በኬኒያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ በድሬዳዋ ለአቅመ ደካማ ወገኖች ያስገነቧቸውን መኖሪያ ቤቶች ለተጠቃሚዎች አስረክበዋል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ(ዶ/ር) እና የሚኒስቴሩና የተጠሪ ተቋማት ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ከድር ጁሃር በተገኙበት ዘመናዊ ቤቶቹ ተመርቀው ለባለቤቶቹ የርክክብ ሥነ-ሥርዓት ተካሂዷል።
በመርሐ ግብሩ እንደተገለጸው፤ ከ20 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸው 20 ዘመናዊ ተገጣጣሚ ቤቶችን ያስገነቡት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እና በኬኒያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ከድሬዳዋ አስተዳደር ጋር በመተባበር ነው።
ከቤቶቹ በተጨማሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በ2 ሚሊዮን ብር የተገዙ የተማሪዎች የመማሪያ ቁሶችን በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ለሚገኙ ቤተሰብ ተማሪዎች ማስረከቡን ኢዜአ ዘግቧል።