Search

የቁልቢ የቅዱስ‎ ገብርኤል ንግስ በዓል በስኬት መጠናቀቁን የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አስታወቀ

እሑድ ታኅሣሥ 19, 2018 115

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት ተከታዮች ዘንድ በታላቅ ድምቀት የሚከበረው የቁልቢ ቅዱስ ገብርኤል የንግሥ በዓል ያለ አንዳች ችግር መጠናቀቁን የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የምሥራቅ ፈጥኖ ደራሽ ፖሊስ የኦፕሬሽን ምክትል መምሪያ ኃላፊ ኮማንደር ታደሰ ሲሳይ ገልጸዋል።
ኮማንደሩ አያይዘውም፣ በዓሉ ፍጹም ሰላማዊ ሆኖ እንዲከበር የፌደራል ፖሊስ ምሥራቅ ፈጥኖ ደራሽ ከሌሎች የፌደራልና የክልል የጸጥታ አካላት ጋር በቅንጅት በመሥራት የተጣለበትን ግዳጅ በብቃት መወጣቱን አስታውቀዋል። በዓሉ በስኬት እንዲጠናቀቅ የራሳቸውን ድርሻ ላበረከቱ የቤተክርስቲያኗ አባቶችና ለአካባቢው ማኅበረሰብም ምስጋና አቅርበዋል።
በተጨማሪም፣ በዓሉ በሚከበርበት አካባቢ ወንጀል በሚፈጽሙ ተከሳሾች ላይ አፋጣኝ ውሳኔ ለመስጠት የተቋቋመው ፈጣን ጊዜያዊ ችሎት፤ የመኪና ዕቃዎችንና የሞባይል ስልኮችን የሰረቁ ተከሳሾች ላይ የእስር ቅጣት ውሳኔ ማስተላለፉን ኮማንደር ታደሰ ሲሳይ ጨምረው ገልጸዋል።