Search

የኢትዮጵያ የባሕር በር ባለቤትነት ለጎረቤት ሀገራት ያለው ፋይዳ

Aug 11, 2025

 ኢትዮጵያ የባሕር በር ባለቤት መሆኗ ለጎረቤት ሀገራት ጭምር ፋይዳው የጎላ መሆኑን ምሁራን ገልጸዋል፡፡

 የባሕር በር ለአንድ ሀገር ብሎም ለአጎራባች ሀገራት ሰፊ ጥቅም የሚሰጥ ነው ሲሉ ከኤፍ ኤም አዲስ 97.1 ጋር ቆይታ ያደረጉ ምሁራን ተናግረዋል፡፡

 የታሪክ ተመራማሪው ፕሮፌሰር አደም ካሚል ለኢትዮጵያ የባሕር በር አስፈላጊነት ወሳኝ ደረጃ የደረሰበት ጊዜ መሆኑን ጠቅሰው፤ ጠቀሜታው ለጎረቤት ሀገራት ጭምር ነው ብለዋል፡፡

 የኢትዮጵያ የስልጣኔ መሰረት ቀይ ባሕር እንደነበር ያስታወሱት ፕሮፌሰር አደም ኢትዮጵያ ወደ ገናናነቷ እንድትመለስ እንዲሁም ዜጎች የተሻለ ኑሮ አስተማማኝና ደህንነቱ የተጠበቀ የባሕር ባር ያስልፈጋታል ብለዋል፡፡

 በወቅቱ ኢትዮጵያ የራሷን ምርት ለተለያዩ ዓለም ሀገራት በቀይ ባሕር በኩል ታቀርብ እንደነበረም አንስተው፤ የቀጣናው ምርት የተሳለጠ እንደነበርም አስታውሰዋል፡፡

 ደራሲ እና የታሪክ ተመራማሪው ጥላሁን ጣሰው በበኩላቸው፤ የኢትዮጵያ የባሕር በር ማግኘት ጠቀሜታው ለኢትዮጵያውያን ብቻ ሳይሆን ለመላው ምስራቅ አፍሪካ ሀገራት ጭምር መሆኑን ተናግረዋል፡፡

 

 ከጎረቤት ሀገራት ጋር በሚኖር የንግድ ልውውጥ እና የባሕር በር አገልግሎት የቀጣናው ሀገራት የጋራ ተጠቃሚ እንደሚሆኑ አንስተዋል፡፡ 

 ኢትዮጵያ በሴራ ከቀይ ባሕር እንድትርቅ መደረጉን ገልጸው፤ ከትርጊቱ ጀርባ ያሉ ሀገራት የኢትዮጵያን አንድነት እና እድገት የማይፈልጉ መሆናቸውንም ገልጸዋል፡፡

 በተባበሩት መንግስታት የባሕር በር የሌላቸው ታዳጊ ሀገራት ጉባኤ፣ የባሕር በር የሌላቸው ሀገራት የሚደርስባቸውን እንግልት እና ችግር በጋራ መፈታት እንዳለባቸው አቅጣጫ መቀመጡን በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት   የውጭ ግንኙነት እና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ ፈትሂ ማሕዲ (ዶ/ር) ተናግረዋል፡፡

 የሕልውና ጉዳይ የሆነው የባሕር በር ለማግኘት  በሚደረገው ሁሉን አቀፍ ጥረት መንግስት በዲፕሎማሲ መስክ ከሚሰራው ባሻገር፣ ዜጎች ለጉዳዩ ትኩረት ሰጥተው የሀገርን ብሔራዊ ጥቅም ማስጠበቅ እንዳለባቸው ነው   ፈትሂ ማሕዲ (ዶ/ር) ያስገነዘቡት፡፡

 በሜሮን ንብረት