Search

የክሪስታል ፓላስ ይግባኝ ጥያቄ ውድቅ ሆነ

Aug 11, 2025

ክሪስታል ፓላስ ከአውሮፓ ሊግ ተሳትፎው ጋር በተያያዘ ያቀረበውን ቅሬታ የዓለም አቀፉ ስፖርት ገላጋይ ፍርድ ቤት ውድቅ አድርጎታል።

የደቡብ ለንደኑ ክለብ ክሪስታል ፓላስ ባለፈው የውድድር ዘመን የኤፍኤ ዋንጫን በማሸነፍ ለአውሮፓ ሊግ ብቁ የመሆን ዕድል አገኝቶ እንደነበር ይታወቃል።

ነገር ግን በክሪስታል ፓላስ ድርሻ ያላቸው አሜሪካዊው ባ ጆን ቴክስተር የክለብ ሊዮን አብዛኛው ባለድርሻ በመሆናቸው አንደኛው ክለብ ብቻ ለአውሮፓ ሊግ ብቁ እንደሚሆን ተገልጾ ነበር።

በዚህም ሊዮን ለአውሮፓ ሊግ ተሳትፎ ብቁ በመሆኑ ክሪስታል ፓላስ በቀጣይ ውድድር ዓመት በአውሮፓ ኮንፈረንስ ሊግ ላይ የሚሳተፍ ይሆናል።

በክሪስታል ፓላስ ቦታ የኮንፈረንስ ሊግ ተሳታፊ የነበሩት ኖቲንጋም ፎረስቶች ደግሞ ከፍ ብለው በዩሮፓ ሊግ ላይ የሚሳተፉ ይሆናል።