Search

ከስደት መልስ ወደኢንቨስትመንት የገባችው ስኬታማ አርብቶ አደር

Aug 11, 2025

ሞሚና ጀማል በስደት ለሥራ የሄደችበት ዐረብ ሀገር ላይ አሰሪዎቿ የእርባታ ሥራ ይሰሩ እንደነበር ታስታውሳለች።

ያኔ እኔም ሀገሬ ስገባ የእንስሳት እርባታውን እጀምራለሁ ብላ አቀደች።

ከስደት መልስ ሞሚና ጥሪቷን እንደቋጠረች ያቀደችውን በሀገሯ ለመከወን ዝግጅት አደረገች።

 



በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ቤንች ሸኮ ዞን ጉራ ፈርዳ ወረዳ እንስሳት በማድለብ እና የወተት ላሞችን የማርባት ሥራ በመጀመር በሀገሬ ሰርቼ መለወጥ እችላለሁ የሚለውን ሃሳቧን ዕውን ማድረግ ችላለች።

ሰርቶ ለመለወጥ ካላት ፍላጎት የተነሳ ከእንስሳት ማድለቡ ጎን ለጎን የእንስሳት ተዋጽዖ መሸጫ መደብር በመክፈት ወደ ሥራ ግብታለች። ይህም ውጤት እንዳመጣላት ነው የምትናገረው።

ከወተት ላሞች ባሻገር ንብ በማነብ፣ በጎችን እና ፍየሎችን እንዲሁም ዶሮ በማርባትም እየሰራች እንደምትገኝ ወ/ሮ ሞሚና ተናግራለች፡፡

ከዐረብ ሀገር ሰርታ ባገኘችሁ ገንዘብ የጀመረችው ሥራ በአንድ ዓመት ውስጥ በሚሊዮኖች ትርፍ እንዳስገኘላት ነው የምታስረዳው።

ለረዥም ጊዜ ከነበረችበት የስደት ኑሮ ተመልሳ በአካባቢዋ ሥራ ፈጥራ በመንቀሳቀስ ከእራሷ አልፎ ለሌሎችም የሥራ እድል መፍጠሯንም ገልጻለች።

 


በቢታኒያ ሲሳይ

#EBC #ebcdotstream #Animalfarming #jobcreation