Search

በዲጂታል ቴክኖሎጂ የላቀ የጤና ዘርፍ ዕውን ማድረግን ያለመው 2025 ሄልዝ ቴክ ፖሊሲ ጉባዔ

ማክሰኞ ነሐሴ 06, 2017 146

 

በዲጂታል ቴክኖሎጂ የላቀ የጤና ዘርፍ ዕውን ማድረግን ያለመው 2025 ሄልዝ ቴክ ፖሊሲ ጉባዔ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው።

3ኛው የሄልዝ ቴክ ስብሰባ 17 የአፍሪካ ሀገራት የጤና ሚኒስትር ተወካዮች፣የዘርፉ አመራሮች እና ባለሙያዎች በተገኙበት በመካሄድ ላይ የሚገኘው።

ጉባዔው እንደ አህጉር በአንድነት የጤናውን ዘርፍ በፈጠራ እና በቴክኖሎጂ ለመምራት እና ወደ ፖሊሲ ትግበራ ለመግባት የሚያስችል ነው ተብሏል።

ጉባዔው ሀገራት ወደ ዲጂታሉ ዓለም በሚያደርጉት ሽግግር፤ የጤናውን ዘርፍም ወደ በዲጂታል ቴክኖሎጂ የላቀ እንዲሆን ልምድ የሚገኝበት መሆኑም ነው የተነሳው።

የፖሊሲ አውጪዎች ፣የዘርፉ ባለሙያዎች እና የጤናው ዘርፍ አመራሮች በጋራ በመሆን፤ ዘርፉን ወደ ዲጂታል ለማሸጋገር አስቻይ ፖሊሲ ለማውጣትም ጉባዔው ያግዛል ተብሏል።

የዘርፉ አመራሮች እንደ አህጉር ከአፍሪካ በሽታ መከላከል እና መቆጣጠር ማዕከል ጋር በጋራ በመሆን ሊሰሩባቸው የሚችሉትን መስኮች ለመለየት እንደሚያስችልም ነው የተገለጸው።

 

በመስከረም ቸርነት