በ2017 በጀት ዓመት 3 ሚሊዮን ያህል እናቶች በጤና ተቋማት የወሊድ አገልግሎት ማግኘታቸውን የጤና ሚኒስቴር ገለጸ።
የጤና ሚኒስቴርና የክልል ጤና ቢሮ አመራሮች የጋራ የምክክር መድረክ በሐረር በመካሄድ ላይ ይገኛል።
የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ በዚሁ ወቅት በ2017 በጀት ዓመት በጤናው ዘርፍ በርካታ ተግባራት ተከናውነዋል ብለዋል።
በበጀት ዓመቱ ዘርፉ ፈታኝ በሆኑ ሁኔታዎች ውስጥ ያለፈ ቢሆንም፤ ለህብረተሰቡ ተገቢውን የጤና አገልግሎት ተደራሽ ማድረግ ተችሏል ሲሉ ተናግረዋል።
መድረኩ በ2017 በጀት ዓመት የተከናወኑ ተግባራትን አፈፃፀም በመገምገም በቀጣይ ለሚከናወኑ ሥራዎች አቅጣጫ ለማስቀመጥ ያለመ መሆኑ ተጠቁሟል።
በሪፖርቱም በ2017 በጀት ዓመት ከ17.6 ሚሊዮን በላይ ዜጎች የቤተሰብ እቅድ አገልግሎት ተጠቃሚ መሆናቸው ተገልጿል።
የቅድመ ወሊድ ክትትል 4 ጊዜ እና ከዚያ በላይ ያገኙ ነፍሰ ጡሮችን 84 በመቶ ማድረስ የተቻለ ሲሆን፤ ይህም ከባለፈው ዓመት ጋር አንፃር የ6 በመቶ ጭማሪ እንዳለው ተጠቅሷል።
በበጀት ዓመቱ በአጠቃላይ ከ233 ሚሊዮን በላይ ዜጎች በጤና ተቋማት አገልግሎት ማግኘታቸው በሪፖርቱ ተመላክቷል።
በቴዎድሮስ ታደሰ
#ኢቢሲ #ኢቢሲዶትስትሪም #ጤናሚኒስቴር #አፈፃፀም