Search

የአውሮፓ የአሸናፊዎች አሸናፊ ዋንጫ ፒኤስጂ ከ ቶተንሀም ሆትስፐር

Aug 13, 2025

በአውሮፓ የሸናፊዎች አሸናፊ ዋንጫ ዛሬ ፒኤስጂ ከቶተንሀም ሆትስፐር የሚገናኙበት ጨዋታ ይጠበቃል፡፡
የዩሮፓ ሊግ አሸናፊው እና የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ አሸናፊው የሚገናኙበት ጨዋታ ምሽት 4 ሰዓት ላይ ይጀመራል፡፡
በጣልያን ብሉነርጂ ስቴዲየም በሚደረገው ጨዋታ በፒኤስጂ በኩል ጃኦ ኔቪስ በቅጣት የማይሰለፍ ሲሆን ዋረን ዛየር ኢምሪ እሱን ተክቶ ወደ ሜዳ የሚገባ ተጫዋች ይሆናል፡፡
ግብ ጠባቂው ጂያንሉጂ ዶናሩማ ከስብሱቡ ውጭ መሆኑ ይታወቃል፡፡
የፊት መስመሩን ኡስማን ዴምቤሌ፣ ኪቪቻ ካቫርስኬሊያ እና ዲዘር ዱዌ እንደሚመሩት ይጠበቃል፡፡
ዘጠኝ ተጫዋቾችን ለባሎንዶር ዕጩ አድርጎ ያስመረጠው ፒኤስጂ በዓለም ክለቦች ዋንጫ ፍጻሜ በቼልሲ ከተሸነፈ በኋላ ለመጀመርያ ጊዜ የሚያደርገው ጨዋታ ይሆናል፡፡
ማንችስተር ዩናይትድን በማሸነፍ የዩሮፓ ሊግ ዋንጫን ያነሳው ቶተንሀም ሆትስፐር በቅድመ ውድድር ጨዋታዎች ደካማ እንቅስቃሴ ያደረገ ሲሆን ዛሬም ከአውሮፓ ሻምፒዮኑ ሌላ ፈተና ይጠብቃዋል፡፡
አንጌ ፖስቴኮግሉን በመተካት ሰሜን ለንደን የረሱት አሰልጣኝ ቶማስ ፍራንክ የውድድር ዓመቱን በድል ለመጀመር በጣልያን ከፈረንሳዩ ሀብታም ክለብ የሚፋለሙ ይሆናል፡፡
በአንተነህ ሲሳይ