Search

የቢሾፍቱ አውሮፕላን ማረፊያ ፕሮጀክት ለአፍሪካ አቪዬሽን ጨዋታ ቀያሪ ነው - የአፍሪካ ልማት ባንክ ፕሬዚዳንት

Aug 13, 2025

የቢሾፍቱ አውሮፕላን ማረፊያ ፕሮጀክት ትልቅ ማሰብ መቻል የወለደው ሜጋ ፕሮጀክት እንደሆና እና ለአፍሪካ አቪዬሽን ጨዋታ ቀያሪ መሆኑን የአፍሪካ ልማት ባንክ ፕሬዚዳንት አኪንውሚ አዴሲና ገልጸዋል።

ፕሮጀክቱ ለአፍሪካ አቪዬሽን ዘርፍ የለውጥ እጥፋት ነው ያሉት ፕሬዚዳንቱ፣ ይህም ከፍ ሲል በዓለም አቀፍ ደረጃ ተፅዕኖ ለመፍጠር የሚያስችል መሆኑን ተናግረዋል።

የላቀ ሐሳብ ከፍተኛ ገንዘብም እንደሚጠይቅ ጠቁመው፣ የአፍሪካ ልማት ባንክ የኢትዮጵያ አየር መንገድን ከፍተኛ ሕልም እውን ለሚያደርገው ፕሮጀክት እገዛ ማድረግ መቻሉ እንዳስደሰታቸው ገልጸዋል።

100 ሚሊዮን መንገደኞችን ከ3 ሺህ 900 ሄክታር በላይ በሆነ ቦታ ለማስተናገድ ሲታሰብ በቦታው ላይ የነበሩ ነዋሪዎች እንደሚነሡ እሙን መሆኑን አንሥተዋል።

ሆኖም ፕሮጀክቱ "የልማት ተነሺዎችን ሕይወት የሚቀይር ልማት" ስለመሆኑ አመላክተዋል።

ለተነሺዎች የታቀደው ካሣ ፍትሐዊ እና በሚገባቸው ልክ መሆኑ የሚያስመሰግነው እንደሆነ በመጠቆም ስለተዘጋጀው አማራጭ ያላቸውን አድናቆት ገልጸዋል።

ፕሬዚዳንቱ በዚህ መሰል ልማት ወደፊትም አጋርነቶች እንደሚቀጥሉ አረጋግጠዋል።

በአፎምያ ክበበው

#etv #EBC #ebcdotstream #ethiopianairlines #AfDB