በቢሾፍቱ ከተማ ሐምሌ 28 ቀን 2017 ዓ.ም በጣለው ኃይለኛ ዝናብ ሳቢያ ከባድ እና ቀላል ጉዳት መድረሱን የቢሾፍቱ ከተማ አስተዳደር የቡሳ ጎኖፋ ጽ/ቤት ኃላፊ አሚና አባ ሂንሰርሙ ለኢቲቪ ተናግረዋል።
ዝናቡ በመኖሪያ ቤቶች፣ በሆራ አርሰዲ በሚገኙ ተክሎች፣ በ10 የአበባ ፋብሪካዎች፣ በ12 ት/ቤቶች፣ በቱሪስት መዳረሻዎች እንዲሁም መንግሥታዊ እና መንግሥታዊ ባልሆኑ ተቋማት ላይ ቀላል እና እና ከባድ ጉዳት አድርሷል ብለዋል።
የከተማዋ ማህበረሰብ ተጎጂ ቤተሰቦች እንዳይቸገሩ እና ንብረታቸው እንዳይበተን የሚመሰገን ተግባር ማከናወኑን ገልፀዋል።
ቢሾፍቱ የዓለም አቀፍ ብሎም የሀገር ውስጥ ቱሪስቶች መዳረሻ መሆኗን ያነሱት ኃላፊዋ፤ ጉዳቱ በዘርፋ ላይ ጥላ ያጠላ መሆኑን ጠቁመዋል።
የተጎዱ መሠረተ ልማቶችን መልሶ ለመገንባት እየተሰራ መሆኑን ጠቅሰው፤ በሂደቱ ሁሉም እንዲሳተፍ ጥሪ አቅርበዋል።
በተያዘው የክረምት ወቅት የጎርፍ አደጋ ቀደም ብሎ ማጋጠሙን የገለፁት የአደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ነሲቡ ያሲን፥ በአንዳንድ አካባቢዎች ዝናቡ መጠነኛ ቢሆንም ባላቸው መልከዓ ምድር ሳቢያ ወደ ጎርፍ እንደሚቀየር ጠቅሰዋል።
የዓለም ነባራዊ የዓየር ሁኔታም ለጎርፉ መከሰት ሌላው መንስዔ መሆኑን ኮሚሽነሩ ተናግረዋል።
"የትኞቹ አካባቢዎች ተጋላጭ ሆነዋል?" የሚለውን የመለየት እና ከባለድርሻ አካላት ጋር በትብብር ምላሽ የመስጠት ሥራ እየተከናወነ ስለመሆኑ ተናግረዋል።
በአፎሚያ ክበበው
#EBC #EBCdotstream #Bisoftu #Floods #Restoration